ዘወረደ

የ1ኛው ሳምንት ትውስታ
በዚህ ሳምንት ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስቦት እኛን የጠፋነውን በጎቹን (የሰው ልጆችን) ፍለጋ  ከሰማየ ሰማያት መውረዱን የምናስታውስበት ነው፡፡ 
የፍቅር አምላክ ቀጠሮውን ሳያፋልስ ለሰው ልጆች በሰጠው የ5500 ዘመን ፍጻሜ ሲደርስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደልን (ገላ 4፡4)፡፡ ይህን ዘመን ብዙዎች ሊያዩ ተመኝተው “እግዚአብሔር ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ” (ዘፍ 49፡8) እያሉ ዐረፍተ ዘመን ስለገደባቸው፤ ነቢያቱም በጸሎታቸው “እጅህን ከአርያም ላክ አድነኝም” (መዝ 143/144/፡7-8) እያሉ አልፈዋል፡፡ በምኞት እንደነበሩ ጌታ “እውነት እላችኋለሁ፥ ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም” ብሏል (ማቴ13፡17)፡፡ 
እኛ ክርስቲያኖች ግን ከአረጋዊ ስምዖን ጋር “ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋል” ማለት ችለናል (ሉቃ 2፡30-31)፤ ስለዚህም ዕድለኞች ነንና፣ በደስታ ለእኛ ሲል መምጣቱትን ለማዘከር “ዘወረደ” በሚል ስያሜ ሳምንቱን ሰይመን፤ ስለ መውረዱ ወንጌል እንሰብካለን፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top