የተምሮ ማስተማር አሻራ ፫ አባ ናትናዔል

የተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት ስለብጹዕነታቸው ባሳተመው ጽሑፍና እርሳቸውም በሰጡት ቃለ መጠይቅ  አቡነ ናትናዔል ከአባታቸው ገብረሕይወትና ከእናታቸው ወለተ ክርስቶስ በ1923ዓ.ም በትግራይ ክልል ነው የተወለዱት፡፡የዓለምስማቸውካህሳይነበርሥመክርስትናቸውደግሞወልደገብርኤል፡፡

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የቅዱስ ሲኖዶሰ አባልና የአርሲ ሀገረ ስበከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ቤተክርስትያንን አገልግለዋል፡የያኔው ካህሳይ ገና የሁለት ዓመት ልጅ እያሉ ነው አባታቸውን በሞት የተነጠቁት፡፡አቡነ ናትናኤል በብርሃንሆነው የተፈጠሩ ነበሩና በጊዜው ባልተለመደ ሁኔታ ገና በ03ዓመታቸው ውዳሴ ማርያምን መልክዐ ማርያምና  መልክዐ ኢየሱስን አጥንተው ጨርሰዋል፡፡

“ከእንጨት መርጦለታቦት፡ ከሰው መርጦ ለሹመት! እንዲሉ አቡነ ናትናኤል በ1935 ዓ.ም ገና በ05  ዓመታቸው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አቡነ ቄርሎሰ ከተባሉ ግብፃዊ ሊቀ ጳጳስ እጅ ማዕረገ ዲቁና ተቀበለዋል፡፡ከዚያም በኋላ ለቤተክርስቲያን ትምህርት በነበራቸው ከፍተኛ ጉጉት በሀገራችን አሉ በተባሉዋና ዋና የአብነት ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር ከታወቁ መምህራን ጾመ ድጓ ዳዊት ምዕራፍ ቅኔ መጻሐፍተ ሐዲሳት ብሉያትና የመሳሳሉትን የሃይማኖት ትምህርቶች ጠንቅቀው ተምረዋል፡፡ ብፁዕ አባታችንን ለየት የሚያደርጋቸው በትምህርት ቤት በነበሩበት ጊዜ ለጥናት እንዲረዳቸው ፍትሐ ነገሥት ውዳሴ ማርያምና ሌሎችንም ትርጓሜዎች በእጅ ጽፈው ለታሪክ ማስቀመጣቸው ነው፡፡

በ1940ዎቹ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ውስጥ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው መምህራን ውስጥ ኢየሱሳውያን (Jesuits)ነበሩበትና ከተሰጣቸው ኅላፊነትና ግዴታ ውጭሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ለተማሪዎቻቸው ያስተምሩ ስለነበር በወቅቱ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ የሆኑና የሃይማኖት ትምህርት የተማሩ ወጣት ተማሪዎች ከነዚህ መምህራን ጋር ክርክር ያደርጉ ስለነበር ይህም ከንጉሡ ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጆሮ በመድረሱ በሁኔታው አዝነው ሃይማኖታዊ ትምህርት እየሠጠ ወጣቶቹን የሚመክር እና የሚያጽናና ሰው ሲፈለግ የዚያን ጊዜው አባ መዐዛ ቅዱሳን የዛሬው አቡነ ናትናኤል ተገኙ፡፡ በዚህ አጋጣሚ በተፈሪ መኮንን ት/ቤት ከ09)$9ዓ.ም ጀም’ሮ በመምህርነት ተቀጥረው ማሰተማር ጀመሩ ይህ አጋጣሚ የተምሮ ማሰተማር ማኅበር ስያሜውን አግኝቶ አገልግሎቱን ሲያስፋፋ ትልቅ አስተዋፅኣ ካደረገት የማኅበሩ መስራቾች ወይንም ቀደም ሲል ከነበረው ቀሪ የህበዕ ማኅበር አባላት ጋር እንዲተዋወቁ እድልን ሰጥቶአቸዋል፡፡ ማኅበሩ ተምሮ ማሰተማር በሚለው ስያሜ ከመሠረቱት ወጣቶች መካከል አነዱና ዋናው ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ነበሩ፡፡ለዘመናዊ ትምህርት ቁብ ያልነበራቸው አቡነ ናትናኤል በጊዜውበነበረው ተጨባጭ ሁኔታ በቅድሰት ሥላሴ አዳሪ ት/ቤት ገብተው እስከ5ኛ ክፍለ ተምረዋል፡፡ በመቀጠልም በአቶ ከበደ ሚካኤል ጉትጎታና ምክር 0ኛ ክፍል ድረስ ተፈሪ መኮንን ት/ቤት ተምረዋል፡፡ ለከፍተኛ ትምህርትም  ወደ ኢየሩሳሌም ተልከው በወቅቱ የአንጀሊካን ቤተክርስቲያን ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ጋር ትመሳሰለች በሚል ግምት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እድል ስለተሰጣቸው “St. George college” ገብተው በ09)^7 ዓ.ም የቤተ ክርስትያን አስተዳደርን በተመለከተ ለሁለት ዓመታት ተምረው ዲኘሎማ አግኝተዋል፡፡ በእንግሊዝ አገር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በ ኤክስኘርመንታል ሳይኮሎጂ ተመርቀዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ የጥምቀት በዓል በጃንሜዳ ሲከበር የበዓሉ መንፈሳዊነት ተዘንግቶ በዘፈንና በጭፈራ ብቻ መከበሩና ባህላዊ ይዘት መያዙ ቁጭት ካሳደረባቸው ሌሎች የቤተክርስቲያን ልጆች ጋር በአይነቱ የመጀመሪያ የነበረውንና አሁን ያለውን መንፈሳዊ ይዘት እንዲይዝ ያደረጉ ታላቅ አባት ነበሩ፡፡

በተምሮ ማሰተማር ፈር ቀዳጅነት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ለማሳካት ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ምንጊዜም ሲታወስ የሚኖር ነው፡፡09)& ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ደርግ ይከተለው በነበረው ርዕዮተ ዓለም በመላ ሀገሪቱ ወጣቶች በቀይ ሽብር ሲያልቁ የወጣቶች መሰብሰቢያ ነው በሚል ተምሮ ማሰተማር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ትኩረት ስለነበር ወጣቶችን በመምከርና በማፅናናት የማኅበሩ አባላት ከጊዜው ማዕበል አንዲተርፉ በማድረጋቸው ደሰታቸው ወሰን አልነበረውም፡፡ ይሁን እንጂ ሦስት አባላት የሳቸውን ምከርና ተግሳፅ ባለ መስማት ለእስር በመዳረጋቸው የሚቆጩበት ነበር፡፡ተምሮ ማስተማር እንደ ማኅበር ይህንያህል ዘመን ሲኖር በዕምነቱ የጸና በየጊዜው እየተነሱ እንደሚጠፉ እንደሌሎች ማኅበራት በሃይማኖት ጉዳይ ስሙ ተነስቶ የማያውቅ በመሆኑ ኩራታቸውአጥፍ ድርብ ነበር፡፡ (ምንጭ:- ተምሮ ማሰተማር ማኅበር ልዩ እትም መንፈሳዊ ጋዜጣ %3 ኛ ዓመት መታሰቢያ)

ብፁዕ አቡነ ናትናዔል እስከ ይሕወት ፍፃሚያቸው ድረስ ለተምሮ ማስተማር “ሰንበት ት/ቤት” የበላይ ጠባቂና አባት በመሆን ፍቅራቸውና ቡራኬያቸው ሳይለይ በ               ቀን ከዚህች ኃላፊ ዓለም በእግዚአብሔር ፈቃድ ተጠርተው በሊቀጳጳስነት ባገለገሉት አርሲ ሃገር ስብከት የቅዱሳን መዐዛ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ቤተ ክርስቲያን ሙስሊም ክርስቲያን ሳይባል ብዙ ህዝብ በተሰበሰቡበት በክብር ዐርፏል፡፡

Scroll to Top