Category «ሰሞነኛ»

በእምነታቸው ምሰሉአቸው

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! `በእምነታቸው ምሰሉአቸው` ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው” (ዕብራ. 13፡7) ባለው መሠረት እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን የአባቶቻችንን የሐዋርያትን እምነት በመምሰል እነርሱ እንደጾሙት የእመቤታችን የፍልሰትዋን መታሰቢያ በየዓመቱ እንጾማለን፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም በዕለተ እሑድ ጥር 21 …

በዓለ ዕርገት

  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! በዓለ ዕርገት በሦስትነቱ ጉድለት በሌለበት ጽርሐ አርያሙ በማይጎበኝና በሩጫ በማይደረስበት በፍጥነት ሊገኝ በማይችል፤ በልቡ ትዕቢት ያለበት ያየው ዘንድ ፈቅዶ ወደ በሩ ለመግባት በማያሰለጥን፤ በሚያስደነግጥ የነጎድጓድ ብልጭታ እና በሚያስፈራ የመብረቅ ድምጽ እንዲሸሽ በሚያደርግ በእግዚአብሔር ስም በኢየሩሳሌም ሰማያዊትና ምእመናን እና ምእመናት በሚሰበሰቡበት በቤተ ክርስቲያን ዘንድ ምስጋና ይገባዋል መቼም …

አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ

አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ አዘጋጅ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም ስብከተ ወንጌል ክፍል እንደ ቅዱስ ጳውሎስ አገላለፅ ከላይ በርዕሱ እንዱ የተባለው ማን እንደሆነ በአጭሩ ገልፀናል፡፡ሞት ስንል ደግሞ ስንት አይነት ሞት እንዳለ የሰው ልጅስ ለምን ሞት እንደተገባው፣ እንደሚከተለው እናያለን፡፡ እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ ሶስት የሞት አይነቶች አሉ፡፡ እነርሱም፡- 1ኛ. ሞተ ሕሊና /የሕሊና ሞት/ ሞተ ሕሊና የሚባለው፣ …

ዘትንሳኤ

  ዘትንሳኤ ወንጌል፡- ዮሐ 20.1-19 ‹‹በእሁድ ሰንበትም ማርያም መግደላዊት ገና ጨለማ ሳለ ገስግሳ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ አፍ ተነስቶ አገኘች ፈጥናም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ጌታ ኢየሱስ ይወደው ወደነበረው ወደ ዚያ ወደ ሁለተኛው ደቀ መዝሙር መጥታ ጌታዬን ከመቃብር ወሰደዋል የወሰዱበትንም ዐላውቅም አለቻቸው፡፡ ጴጥሮስና ያ ሁለተኛው ደቀመዝሙርም ወጡና ወደ መቃብሩ ሔዱ፡፡ ሁለቱም ባንድነት ሲሮጡ ያ ሌላው …

ሆሣዕና(፰ኛ ሳምንት)

ሆሣዕና ወንጌል ዮሐ.፲፪፥፲፩‐፳ ‹‹በማግስቱም ለበዓል መጥተው የነበሩ ብዙ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በሰሙ ጊዜ የሰሌን ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የባሕርይ አምላክ ነው፤ የእስራኤልም ንጉስ ነው፤ እያሉ ወጥተው ተቀበሉት፡፡ጌታ ኢየሱስም የአህያ ግልገል አግኝቶ በእስዋ ላይ ተቀመጠ፡፡ ‹‹የጽዮን ልጅ አትፍሪ እነሆ! ንጉስሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣል፡፡›› ተብሎ እንደተፃፈ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከተገለጠበት ጊዜ …

ኒቆዲሞስ (፯ኛ ሳምንት)

  ኒቆዲሞስ ወንጌል፡- ዮሐ ፫፥፩‐፲፪ ‹‹ ከፈሪሳውያን ወገን ኒቆዲሞስ የተባለ የአይሁድ አለቃ አንድ ሰው ነበረ፡፡ እርሱ አስቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታ ኢየሱስ መጥቶ እንዲህ አለው፡፡ መምህር ልታስተምር እግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና፡፡ ጌታ ኢየሱስም መልሶ እውነት እውነት እልሀለሁ ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማየት አይችልም አለው፡፡ …

ገብር ኄር (፮ኛ ሳምንት)

  ገብር ኄር ወንጌል፡- ማቴ.፳፭፥፲፬‐፴፩ ‹‹ መንገድ እንደሔደ ሰው ነውና፤ብላቴኖቹን ጠርቶ ሊያተርፋበት ገንዘቡን ሰጣቸው፡፡ አምስት መክሊት የሰጠው አለ፤ ሁለት መክሊት የሰጠው አለ፤ አንድ የሰጠው አለ፡፡ ከነርሱ ለእያንዳንዱ በሚችሉት መጠን ሰጣቸውና ወዲያውኑ ሔደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለው ሔደ ነገዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁ ሁለት የተቀበለውም ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሔደ ምድርንም ቆፈረና …

ደብረ ዘይት (፭ኛ ሳምንት)

    ደብረ ዘይት ወንጌል፡- ማቴ.፳፬፥፩‐፲፭ ‹‹ ጌታ ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ወደርሱ ቀርበው የቤተ መቅደስን የሕንጻውን አሰራር አሳዩት፡፡ ጌታ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፡- ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እነግራችኋለሁ ከዚህ በድንጋይ ላይ ድንጋይ ሳይፈርስ አይቀርም፡፡ በደብረ ዘይትም ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደርሱ ቀረቡና እንዲህ አሉት፡፡ ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለሙ …

ምኩራብ (፫ኛ ሳምንት)

    ምኩራብ ወንጌል፡- ዮሐ ፪፥፲፪ ‹‹ከዚህም በኃላ እርሱ፣ እናቱ፣ ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም ወርደው በዚያ ጥቂት ቀን ተቀመጡ፡፡ ብዙም አይደለም የአይሁድም የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በምኩራብም ላሙን፣ በጉን፣ ርግቡን የሚሸጡትን የሚገዙትንም አገኘ፤ ለዋጮችንም ተቀምጠው ከገመድ የተሰራ አለንጋ አበጀ በጉንም ላሙንም ሁሉንም ከምኩራብ አስወጣ፤ የለዋጮችንም ወርቅ በተነ፤ መደርደሪያቸውንም አፈረሰ፤ …

ቅድስት (፪ኛ ሳምንት)

    ቅድስት (፪ኛ ሳምንት) ወንጌል፡- ማቴ ፮.፲፮-፳፭ ‹‹በምትጾሙበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ፡፡ እነርሱ እንደ ጾሙ ሰው ያውቃቸው ዘንድ ይጠወልጋሉና፤ ግንባራቸውንም ይቋጥራሉና መልካቸውንም ይለውጣሉና ፡፡ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀበሉ፤ እናንተስ በምትጾሙበት ጊዜ ራሳችሁን ቅቡ፡፡ ፊታችሁን ታጠቡ እንደ ጾማችሁ ሰው እንዳያውቅባችሁ የተሰወረውን ከሚያውቅ በሰማይ ካለ አባታችሁ በቀር በስውር የሚዐያችሁ አባታችሁም ዋጋችሁን በግልጥ ይሰጣችኋል፡፡የሚያልፈውን፣ ብል ነቀዝ የሚያበላሸውን …

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro