ገብር ኄር (፮ኛ ሳምንት)

 
ገብር ኄር

ወንጌል፡- ማቴ.፳፭፥፲፬‐፴፩
‹‹ መንገድ እንደሔደ ሰው ነውና፤ብላቴኖቹን ጠርቶ ሊያተርፋበት ገንዘቡን ሰጣቸው፡፡ አምስት መክሊት የሰጠው አለ፤ ሁለት መክሊት የሰጠው አለ፤ አንድ የሰጠው አለ፡፡ ከነርሱ ለእያንዳንዱ በሚችሉት መጠን ሰጣቸውና ወዲያውኑ ሔደ፡፡ ያ አምስት መክሊት የተቀበለው ሔደ ነገዶም ሌላ አምስት መክሊት አተረፈ፡፡ እንዲሁ ሁለት የተቀበለውም ሌላ ሁለት አተረፈ፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው ግን ሔደ ምድርንም ቆፈረና የጌታውን ወርቅ ቀበረ፡፡ ከብዙ ቀንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ ተመልሶ ተሳሰባቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለውም ቀረበና አቤቱ አምስት መክሊቶችን ሰጠኸኝ፤ እነሆ! ሌላ አምስት አተረፍኩ ብሎ አምስት መክሊቶችን አመጣ፡፡ ጌታውም አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንክ ስለሆንክ በብዙ እሾምሀለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም መጥቶ አቤቱ ሁለት መክሊቶች ሰጥተኸኝ አልነበረምን? እነሆ! ሌሎች ሁለት መክሊቶች አትርፌአለሁ አለ፡፡ ጌታውም አንተ የታመንክ በጎ አገልጋይ በጥቂቱ የታመንክ ስለሆንክ በብዙ እሾምሀለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ አንድ መክሊት የተቀበለው መጣና እንዲህ አለ፡፡ አንተ ጨካኝ ሰው እንደሆንክ ዐውቃለሁ፤ ካልዘራህበት ታጭዳለህ፡፡ ካልበተንክበት ትሰበስባለህ፡፡ ስለፈራሁም ሔድኩና መሬት ቆፍሬ ወርቅህን በምድር ውስጥ ቀበርኩ፡፡ እንግዲህ እነሆ! ገንዘብህ፡፡ጌታው መልሶ አለው አንተ ክፉ ሰነፍ ባርያ እኔ ጨካኝ ሰው ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንኩት የምሰበስብ፣ እንደሆንኩ ታውቀኛለህን? ወርቄን ወደ ሳጥኔ ልትመልስ በተገባህ ነበር፡፡ እኔ ራሴም መጥቼ በትርፍ ባሰራሁት ነበር፡፡ ከዚያ የቆሙትንም እንዲህ አላቸው፡፡ይህን መክሊት ከሱ ተቀብላችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ሁሉ ይሰጡታል፤ ይጭምሩለታልና፤ ለሌላው ግን ያንኑ ያለውንም ቢሆን ይወስዱበታልና ክፉውን ሰነፍ ባርያ ግን ወደ ውጭ አውጥታችሁ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት በአለበት በጨለማ ወህኒ ቤት አግዙት፡፡››
ዋና መልእክት
•ሰው እግዚአብሔርን የገለጠለትን ህግ መፈጸም በታላቅ ጉባኤ ፊትም መመስከር ማስተማር ይጠበቅበታል፡፡
•ማናቸውም ባለሙያ የተሰጠውን አደራ በታማኝነትና ትጋት መጠበቅ ይኖርበታል፡፡
ተጨማሪ መልእክት፡-
•ለካህናት ከተሰጠው አደራ አንዱ ሕሙማንን ሊፈውሱ ሊያጽናኑም ነው፡፡ ስለዚህ በክህነታቸው ሕሙማንን መርዳት ማስረዳትም ይገባቸዋል፡፡
‹‹ብዙ አጋንንትን ያወጡ ነበር፤ ብዙዎችን ድውያንም ዘይት ይቀቧቸው ነበር፤ ይዱኑም ነበር፡፡›› ማር.፮፥፲፫፣ ማቴ.፲፥፰

/መዝሙር ዘገብር ኄር መኑ ውእቱ ገብር ኄር/
፪ኛ ጢሞ.፪፥፩‐፲፮
፩ኛ ጴጥ ፭፥፩‐፲፮
የሐ.ሥ. ፩፥፮‐፱
ምስባክ፡-
መዝ ፴፱፥፰
ከመ እንግር ፈቃደከ መከርኩ አምላኪየ
ወሕግከኒ በማዕከለ ከርሥየ፡፡
ዜኖኩ ጽድቀከ በማኅበር ዐቢይ
ትርጉም፡-

አምላኬ ሆይ ፈቃድህን እናገር ዘንድ ወደድኩ
ህግህም በልቡናዬ አለ፡፡ በታላቅ ጉባኤ ቸርነትህን ተናገርኩ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዓለመ ዓለም አሜን!!!
ምንጭ
ምስባክ ቃለ ሕይወት ሊቀ ጽጉሃን ኄለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሰባቱ አጽዋማት ተስፋዬ ምትኩ

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro