ደብረ ዘይት (፭ኛ ሳምንት)

 

 
ደብረ ዘይት

ወንጌል፡- ማቴ.፳፬፥፩‐፲፭

‹‹ ጌታ ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ወደርሱ ቀርበው የቤተ መቅደስን የሕንጻውን አሰራር አሳዩት፡፡ ጌታ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፡- ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እነግራችኋለሁ ከዚህ በድንጋይ ላይ ድንጋይ ሳይፈርስ አይቀርም፡፡ በደብረ ዘይትም ተቀምጦ ሳለ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደርሱ ቀረቡና እንዲህ አሉት፡፡ ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለሙ ፍጻሜስ ምልክቱ ምንድን ነው? ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡፡ ተጠንቀቁ እንዳያስቱአችሁ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉና፤ ጦርነትን ሰልፍን የጦርነትንም ድምጽ በሰማችሁ ጊዜ ዕወቁ፤ አትደንግጡ፤ እንዲሁ ይሆናልና፡፡ ወዲያው የሚያልፍ አይደለም፡፡ ህዝብ በህዝብ ላይ ነገስታትም በነገስታት ላይ ይነሳሉ፡፡ በየሀገሩ ረኀብ ፣ቸነፈር ንውጽውጽታ፣ጸብ ክርክር ይመጣል፡፡ ይህ ሁሉ የምጥ መጀመሪያ ነው፡፡ ያን ጊዜ ይከሱአችኋል፡፡ ይገድሏአችኋል፡፡ በስሜ ስላአመናችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ የተጣላችሁ ትሆናላችሁ፡፡ ያን ጊዜ ብዙዎች ሃይማኖታቸውን ይለውጣሉ፡፡ እርስ በርሳቸውም ይጣላሉ፤ ይጋደላሉ፡፡ ብዙዎች ሐሰተኞች መምህራን ይመጣሉ፡፡ ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡ ከአመፅና ከክፋት የተነሳም ፍቅር ከብዙዎች ዘንድ ትጠፋለች፡፡ ትዕግስትን ያዘወተረ እርሱ ይድናል፡፡ ይህም የመንግስት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ምስክር ሊሆን ያን ጊዜ ኅልቀት ይደርሳል፡፡››
ዋና መልእክት፡-
•እግዚአብሔር በስጋ ይወለዳል፤በክበበ ትሰብእትም ይመጣል መጥቶም በሥልጣኑ የጻድቃን ዋጋቸውን፣ የኃጥአንንም ቁርጥ ፍርዳቸውን ይሰጣል፡፡
•በዚህ ዓለም የማያልፍ ነገር የለም፡፡ ቁም ነገሩ ለምልክትነት የሚገለፀውን መከራና የክህደት ዜና ታግሦ በሃይማኖት መፅናት ነው፡፡
ተጨማሪ መልእክት
•ሰው ፍቅርን የመሰለ ጸጋ ያጣበት ዘመን በመሆኑ፤ ሰውን ጠልተን እግዚአብሔርን መውደድ ስለምንችል ለሰው ያለንን ፍቅርና ርኅራኄ በቸርነት መግለጽ ይገባናል፡፡
‹‹ወንድሙን የማይወድ፣ እግዚአብሔርን አያውቀውም›› ፩ኛ ዮሐ.፬፥፰ ዮሐ.፲፫፥፴፬‐፴፮

/መዝሙር ዘደብረ ዘይት እንዘይነብር እግዚእነ/
፩ኛ ተሰ.፬፥፲፫
፪ኛ ጴጥ.፫፥፯‐፲፭
የሐ.ሥ.፳፬፥፩‐፳፪
ምስባክ፡-
መዝ49.3

እግዚአብሔር ገሀደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ
ትርጉም፡-
እግዚአብሔር በግልጽ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም አይልም በፊቱ እሳት ይነዳል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዓለመ ዓለም አሜን!!!
ምንጭ
ምስባክ ቃለ ሕይወት ሊቀ ጽጉሃን ኄለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሰባቱ አጽዋማት ተስፋዬ ምትኩ

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro