ይልመድብሽ/ህ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ይልመድብሽ /ህ

(ሁለት ጓደኛማቾች ወደ  ትምህርት ቤት ይሄዳሉ)

በመቅደስ ተ/ያሬድ

ኢዮብ፥ የትናንትናው ዝናብ ደረሰብህ፣ እንዴትስ ሆንህ?

አቤል፥ አዎ  ለትንሽ ደረሰብኝ  ግን ማርቆስ ዣንጥላ ይዞ ነበር አብረን ተጠለልን

ኢዮብ፥       አየህ ዋናው ፍቅሩ ነው የሚሉት አባቶቻችን

ማርቆስ፥ አቤል፣ኢዮብ ጠብቁኝ ጠብቁኝ አብረን እንሂድ

ኢዮብ፥ ና በል ቶሎ  ስንጠራህ እኮ አትሰማም ነበር

ማርቆስ፥ አዎ  አሁን እናቴ ስትነግረኝ ወደ እናንተ መጣሁ

ኢዮብ፥ ማርቆስ ሲመጣ ይነግርሃል ጠይቀው ብሎኝ ነበር ምንድን ነው? እስኪ ንገረን

ማርቆስ፥ ውይ ይልመድብሽ ጨዋታን እኮ ነው

አቤል፥ አዎ ትናንት ሲያስታውሰኝ ቆይ ኢዮብ ባለበት ብዬው ነበር  ቤተ ክርስቲያን ተምረን ነበር እና በጣም ደስ ይለኛል እስኪ        እንነጋገር

ማርቆስ፥ እኔ ልጀምር

ኢዮብ፥ ይቻላል

ማርቆስ፥ ይልመድባችሁ

ኢዮብ እና አቤል፥ ምን

ማርቆስ፥ በማለዳ  ስትነሱ ጨለማውን አሳልፎ  ብርሃንን ለሰጣችሁ ፈጣሪ ምስጋና ማቅረብ

ኢዮብ፥  እሺ እናንተም ይልመድባችሁ

አቤል እናማርቆስ፥ ምን

ኢዮብ፥ ስለ  ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከአባቶች እግር ስር ቁጭ ብሎ  መማር መጠየቅ

አቤል ፥ ይልመድባችሁ

ኢዮብ እና ማርቆስ፥ ምን

አቤል፥ መጸለይ፣ መጾም፣ ለፈጣሪ ምስጋና ማቅረብ እንዲሁም ቅዳሴ ማስቀደስና  ቅዱስ ቁርባን          መቀበል

ማርቆስ፥ ይልመድባችሁ

ኢዮብ እና አቤል ፥ ምን

ማርቆስ፥ ስለ  ቅዱሳን አባቶች ታሪክ መስማትና  እነሱ የሄዱበተን መንገድ መከተል

ኢዮብ፥ ይልመድባችሁ

አቤል እና  ማርቆስ፥ ምን

ኢዮብ፥ የግእዝ ቋንቋን መማር፣ ዳዊት  መድገም፣ውዳሴ ማርያም ማድረስ

ማርቆ ስ፥ ይልመድባችሁ

ኢዮብ እና  አቤል፥ ምን

ማርቆስ፥ በንግግራችሁ፣ በአካሄዳችሁና  በመንገዳችሁ ሁሉ ክርስቶስን  መምሰል

ማርቆስ፥  ደግሞም ይልመድባችሁ

ኢዮብ እና አቤል፥ የእመቢታችንን ፍቅሯን ያሳድርባችሁ ዘንድ ዘወትር በጸሎት መትጋትና  ክብሯን  መመስከ

አቤል፥  ይልመድባችሁ

ኢዮብ እና ማርቆስ፥ ምን

ማርቆስ፥ ስለ  መላእክት ምልጃ፣ ሰለ ጠባቂነታቸውም ጭምር በሚገባ ማወቅ፣ ዝክራቸውን በመዘከር እለታችውን ማክበር

ኢዮብ፥ በጣም ደስ የሚል ትምህርት ነው የተነጋገርነው

አቤል፥ ሁላችንም ሊለምድብን ይገባል

ማርቆስ፥ አዎ  ይህንን ካደረግን ፈጣሪ ልጆቹ ያደርገናል

ኢዮብ ፥ በተስፋ የምንጠብቃትና  በእጅ ያልተሰራች የሰማይ ድንኳን እንደሚያወርሰንም እናቴ  ነግራኛለች

አቤል፥ አሜን ለዛ  ያብቃን

ኢዮብ እና ማርቆስ ፥ አሜን

ማርቆስ፥ በሉ ሰላም ዋሉ ወንድሞቼ እየተነጋገርን ምንም ሳይታወቀን ክፍላችን ደረስን

አቤል፥ በሉ ሰላም ዋሉ ለእረፍት እንገናኝ

/// ወስብሐት ለእግዚአብሔር ///

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro