ማውጫ

ይህን መጽሐፍ ብላ

. . . . . ወዳጄ ሆይ ገንዘብህን ወስደውብሃልን ? “ከእናቴ ማኅፀን ዕራቁቴን ወጥቻለሁ ፤ዕራቁቴን ወደዚህያው እመለሳለሁ ” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር አንብብ /ኢዮ.1.21/፡፡ በዚህም ላይ የሐዋሪያውን ቃል ጨምርበት ፤እንዲህ ያለውን “ወደ ዓለም ያመጣነው የለንምና ከእርሱም ልንወስድ የምንችል የለም” /1ኛ ጢሞ.6.7/፡፡ ሰዎች ሰድበውሃልን ? አንዳንዶቹስ ለመቁጠር እንኳን እስኪታክት ድረስ ነቅፈውሃልን ? እንዲህ የሚሉትን ኃይለ ቃላት አስታውስ፡- “ሰዎች ኹሉ ስለ እናንተ መልካሙን ነገር ቢናገሩላችሁ ወዮላችሁ” /ሉቃ.6.26/ “ ስዎች ክፉ ስም ቢያወጡላችሁ ደስ ይላችሁ ፤ ሐሴትም አድርጉ”  /ሉቃ.6.22 ማቴ 5.11/፡፡ ወደ ባዕድ አገር እንድትሰደዱ አድርገውሃልን ? ጥንቱንም ከአባትህ አገር እየኖርህ እንዳልኾነ ልብ በል፤ምድር መላዋንም እንደ ባዕድ አገር እንድትቄጥራት እያስታወሱህ ነውና ፈቃድህ ለኾነ ጥበበኛ ኹን፡፡ እጅግ የበዛ ስቃይ ያለበት በሽታ አግኝቶሃልን?”. . . . . .

. . . . “ውስጥሽን የሚያስጨንቀው ምንድን ነው? በመራር ኀዘን የተያዝሽውና ልብሽ የተሰበረው ስለ ምን ምክንያት ነው? በቤተ ክርስቲያን ላይ ስለ ደረሰው ጽኑና ጥቁር ማዕበል፣ጨረቃ እንደሌለችበት ሌሊት ኹሉንም  ነገር ጨለማ ሰለ ከደነው፣ ይህም ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ ስለ ሔደ፣እጅግ አስቸጋሪ የኾኑ ኹኔታዎች እየባስባቸው ስለ መጡ፣እንዲሁም ዓለምን እያጠፏት ስለ ኾነ ነውን?”. . . . .

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro