ፋና ወጊው ወልደ ሰማዕት ገብረወልድ

በ፲፱፻፴፱ ዓ.ም በተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት ከ፲፪፻፲ ተማሪዎች መካከል ለትምህርት ከከተሙት አንዱወልደሰማዕትገብረወልድ (አሁን ደጃዝማች) ነበሩ፡፡ ትምህርት ቤቱን የተቀላቀሉት በ፲፱፻፴፮ ዓ.ም ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በአስተማሪነት የነበሩትን መምህራንን ደጃዝማች ወ/ሰማዕት ሲገልጹአቸው በየሙያቸው ጥልቅ የሆነ ዕውቀት የነበራቸው በትምሀርት ክፍልና ከክፍል ውጪ ተማሪውን ለራሱም ሆነ ለአገር ዕድገት የሚጠቅምናአገሩን የሚወድ ዜጋ  እንዲሆን የሚያዘጋጁት ነበሩ፡፡ ተማሪዎች በትምህርትና በሥነምግባር ታንጸው ጽኑ የአገር ፍቅር አድሮባቸው እውነተኛ የሕዝብ አገልጋዮች ሆነው አገራቸውን ማበልጸግ እንዲችሉ ለማድረግ ይሰሩም ነበር፡፡

ተማሪዎችን የሚያስተምሩ የነበሩ እነዚህ መምህራን አቻየማይገኝላቸው ከፍተኛ ዕውቀት የነበራቸው ምሁራንም ነበሩ፡፡ በትምህርት ቤቱ ከፍተኛ ክፍሎች ለሚማሩት ተማሪዎች በክፍል ከሚያስተምሩት መደበኛ ትምህርት በተጨማሪ መምህራን እንደ አማካሪዎች ሆነው ለየአንዳንዳቸው ተመድበውላቸው በሳምንት ሁለት ቀን ማታ ወደ አማካሪያቸው ቤት እየሄዱ ለሁለት ሰዓት ያህል ስለአገር ፍቅርና ሥነምግባር ከትምህርት ቤት ጨርሰው ሲወጡም ሕዝብንና አገርን ማገልገል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ይህንንም ሲፈጽሙ በታማኝነትና በትጋት መሥራት እንዳለባቸው በልዩ ልዩ ዘዴዎች ይመክሯቸውና ያስተምሯቸው ነበር፡፡ አማካሪዎቻችው ሌላው ቀርቶ ወደፊት ሲለሚመሰርቱት ጋብቻና ስለሚኖሯቸውልጆች አሰተዳደግ ጥሩ ዜጋ እንዲሆኑ እንዴት አድርገው እየተንከባከቡ ማሳደግ እንደሚገባቸው ልጆች ከወላጆቻቸው ስለሚማሩት ጭምር ይነግሯቸው እንደነበረ ይገልጸሉ ፡፡ይህንንም አባባል ቀሲስ ታደሠ መንግሥቱ ቃል በቃል በሚመስል ሁኔታ በቃለ ምልልሳቸው ላይ ደግመውታል፡፡

ደጃዝማች ሲቀጥሉም በዚያን ጊዜ በትምህርት ቤት ከተማሯቸው ትምህርቶች ያላነሰ በተለይ ስለ መልካም አስተዳደርና የአገር ፍቅር በልጅነታቸው ከአባታቸው ካገኙት ምክርና ትምህርት በተጨማሪ ከተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት አስተማሪዎቻቸው ከፍ ያለ ግንዛቤና ጥቅም አግኝተውበታል፡፡

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro