የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት አባላት ወደ ዝዋይ ገዳማት ጉዞ አደረጉ፡፡

ቅዳሜ ግንቦት 19 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ በ12፡30 በፀሎት ተከፍቶ የጀመረውን ጉዞ ከገዳሙ ተነስቶ አዲስ አበባን ለቆ በመውጣት የዝዋይ ገብርኤልን ንግስ መሳተፍ የቻለ ሲሆን በዝዋይ ሀይቅ ላይ ያሉትን የደሴት ገዳማት ለመሳለም የቅዱሳንንና የገዳሙን በረከት ተቀብሏል፡፡ በሀይቁ ላይ ለ5 ሰዓታት የጀልባ ጉዞ የተደረገ ሲሆን
1. ጠዴቻ ደብረ አብርሃም
2. አርባዕቱ እንስሳ
3. ደብረ ፅዮን
4. ደብረ ሲና
5. ገሊላ አቡነ ተክለሃይማኖትን በአባቶች ገለፃ በሚገባ ሰለታሪኩ ለመረዳት ተችሏል፡፡ እሁድ ግንቦት 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ተጎዦች ወደ ተነሱበት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የደረሱ ሲሆን ጉዞው እንዲሳካ ለፈቀደው ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋናን በማቅረብ የጉዞው መርሃ ግብር በፀሎት ተዘግቷል፡፡

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro