የተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት ዐውደ-ርእይ ተከፈተ

የተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት ፷ኛ ዓመት ላለፉት ወራት በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ይገኛል፡፡ በያዝነው ሳምንት እሁድ ሚያዚያ ፳፱/ ቀን በልዩ የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱን በዐውደ-ርእይ ዝግጅት፤በብፁዕ አቡነ ሳውሮስ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፉ እና መጋቢ ዕሩያን አባ ኤልያስ በልሁ(ቆሞስ)የምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳሙ ምክትል አስተዳዳሪ እና የተምሮ ማስተማር ሰ/ት/ቤት የበላይ ሰብሳቢ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የሰንበት ት/ቤት አባላት እና ክብር እንግዶች ከቅዳሴ መልስ ተከፍቷል፡፡ የበዓሉ አስናዶች እንደገለጹት ከልጅ እስከ አዋቂ ስለ እምነቱ ማወቅን፤ስለ ዘመኑ ፈተናዎች ምላሽ መነቃቃትን ያሳይ ዘንድ ለ፯ ቀናት ከረፋዱ 3፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ማታ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ገልጸዋል፡፡ክቡራን ምዕመናን፣ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት ሌሎች በማዳረስ እስከ ግንቦት ፮ ቃለ-ወንጌልን እንዲከታተሉ የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤቱ ፷ኛ ዓመት አዘጋጆች ተጋብዘዋል፡፡

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro