ዘትንሳኤ

 
ዘትንሳኤ

ወንጌል፡- ዮሐ 20.1-19
‹‹በእሁድ ሰንበትም ማርያም መግደላዊት ገና ጨለማ ሳለ ገስግሳ ወደ መቃብር መጣች፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ አፍ ተነስቶ አገኘች ፈጥናም ወደ ስምዖን ጴጥሮስና ጌታ ኢየሱስ ይወደው ወደነበረው ወደ ዚያ ወደ ሁለተኛው ደቀ መዝሙር መጥታ ጌታዬን ከመቃብር ወሰደዋል የወሰዱበትንም ዐላውቅም አለቻቸው፡፡ ጴጥሮስና ያ ሁለተኛው ደቀመዝሙርም ወጡና ወደ መቃብሩ ሔዱ፡፡ ሁለቱም ባንድነት ሲሮጡ ያ ሌላው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞት ወደ መቃብር ደረሰ፡፡ በተመለከተም ጊዜ መግነዙን ተቀምጦ ዐየ፤ ግን ወደ ውስጥ አልገባም፡፡ ስምዖን ጴጥሮስም ተከትሎት ደረሰና ወደ መቃብር ገባ፤ ከፈኑንም ባንድ ወገን ተቀምጦ አገኘ፤ በራሱ ላይ የነበረውን መጠምጠሚያም ለብቻው ተጠቅልሎ ከከፈኑ ጋርም አልነበረም፡፡ ከዚህም በኃላ ወደ መቃብር የደረሰው ሌላው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብር ገባ፤ ዐይተውም አመኑ ከሙታን ተለይቶ ይነሳ ዘንድ እንዳለው በመጻሕፍት የተጻፈውን ገና ዐላወቁም ነበርና፤ ከዚህም በኃላ ሁለቱም ተመልሰው ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ ማርያም ግን ከመቃብር በስተውጭ እያለቀሰች ቆማ ነበር፡፡ እያለቀሰችም ወደ መቃብር ውስጥ ተመለከተች፤ ሁለት መላእክትም አንቺ ሴት ምን ያስለቅስሻል ማንንስ ትሺአለሽ? አሉአት፡፡ ጌታዬን ከመቃብር ውስጥ ወስደውታል፤ የወሰዱበትንም ዐላውቅም አለቻቸው፡፡ ይህንም ተናግራ ወደኋላዋ መለስ ብትል ጌታ ኢየሱስን ቆሞ አየችው፡፡ ጌታ ኢየሱስ እንደሆነም አላወቀችም፤ ጌታ ኢየሱስም አንቺ ሴት ምን ያስለቅስሻል ማንንስ ትሽአለሽ? አላት፡፡ እርሱዋ ግን የአትክልት ቦታ ጠባቂ መስሎአት ነበር፤ ጌታዬ አንተ ወስደኸው እንደሆነ ሔጄ ወደ እኔ እንዳመጣውና ሽቱ እንድቀባው የወሰድክበትን ንገረኝ አለችው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ማርያም አላት፤ እርስዋም መለስ ብላ በዕብራይስጥ ቋንቋ ረቡኒ አለችው፡፡ ትርጓሜውም መምህር ማለት ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስም አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሒጂና ወደ አባቴ ወደ አባታችሁ፤ ወደ አምላኬ ወደ አምላካችሁ፤ ዐርጋለሁ በያቸው አላት፡፡ ማርያም መግደላዊትም ሔደች፤ ለደቀመዛሙርቱም የምስራች ነገረቻቸው፤ ጌታችንንም ዐየሁት አለቻቸው፤ እንደ ነገራትም ነገረቻቸው፡፡››
ዋናው መልእክት
•ጌታችን ጠላት ዲያብሎስን ድል ነስቶ ፈጥኖ በሥልጣኑ ተነሳ፡፡
•የጌተሰችንን ውለታና ፍቅር የሚያስብ ሰው በሃይማኖት ጸንቶ ስጋውን ደሙን መቀበል ይገባዋል፡፡
ተጨማሪ መልዕክት
•ሰው ወገኑን እንኳን ታመመ ብሎ ከዚያም በላይ የባሰ ችግር ቢደርስበት ሰብአዊ መብቱን መንፈግ ማግለልም ተገቢ አይደለም፡፡ እንዲህ ቢያደርግ ክርስቲያን አያሰኘውም፡፡ ይልቁንም መርዳት ይገባዋል፡፡
‹‹አንድ ሳምራዊም፣ በዚያች መንገድ ሲሔድ አገኘው፤ ዐይቶም አዘነለት፤ ወደርሱም ቀርቦ በቁስሉ ላይ ወይንና ቅባ ጨመረለት፡፡›› ሉቃ. 10.33-35፣ 1ኛ ጴጥ. 1.22
/መዝሙር ዘትንሳኤ ይትፌሳሕ ሰማይ
ማቴ. 28.1
ማር. 16.1
ሉቃ. 24.1-13
ምስባክ፡- መዝ 77.85
ወተንስአ እግዚአብሔር ከመዘንቃህ እምንዋም
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ
ትርጉም፡-እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ሰው ተነሳ
የወይን ጠጅ ስካር እንዳለፈለት ኃይለኛ ሰውም ጠላቱንም በኋላው ገደለ፡፡
ምንጭ
ምስባክ ቃለ ሕይወት ሊቀ ጽጉሃን ኄለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሰባቱ አጽዋማት ተስፋዬ ምትኩ

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro