ኒቆዲሞስ (፯ኛ ሳምንት)

 
ኒቆዲሞስ

ወንጌል፡- ዮሐ ፫፥፩‐፲፪
‹‹ ከፈሪሳውያን ወገን ኒቆዲሞስ የተባለ የአይሁድ አለቃ አንድ ሰው ነበረ፡፡ እርሱ አስቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታ ኢየሱስ መጥቶ እንዲህ አለው፡፡ መምህር ልታስተምር እግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፡፡ እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ተአምራት ሊያደርግ የሚችል የለምና፡፡ ጌታ ኢየሱስም መልሶ እውነት እውነት እልሀለሁ ዳግመኛ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማየት አይችልም አለው፡፡ ኒቆዲሞስም ሰው ከሸመገለ በኋላ ዳግመኛ መወለድ እንደምን ይቻላል? ዳግመኛ ይወለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅጸን ተመልሶ መግባት ይቻላልን? አለው፡፡ ጌታ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው እውነት እውነት እልሀለሁ ዳግመኛ ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ያልተወለደ ወደ እግዚብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም፡፡ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነውና፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነውና፡፡ ስለዚህም ዳግመኛ ልትወለዱ ይገባችኋል ስለ አልኩህ አትድንቅ፤ ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳልና ድምፁን ትሰማለህ እንጂ ከየት እንደሚመጣ ወዴት እንደሚሔድም ዐታውቅም፡፡ ከመንፈስ ቅዱስም የሚወለድ ሁሉ እንዲሁ ነው፡፡ ኒቆዲሞስም መልሶ አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ ግን ይህን አታውቅም አለው፡፡ የምናውቀውን እንድንናገር በዐየነውም እንድንመሰክር እውነት እውነት እልሀለሁ፡፡ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉንም፡፡››
ዋናው መልእክት፡-
•ሰው ሰውኛውን እንዳልናገር በሌሊት ጠላቴን ከእጄ ጥለህ ፈተንከኝ በደል ግን አልተገኘብኝም፡፡
•የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነቱን አምኖ ያልተጠመቀ ሰው መንግስተ ሰማያት ሊገባ አይችልም፡፡
ተጨማሪ መልእክት
•ሰው በራሱ የሚያውቀውን ምስጢር እንደ አስፈላጊነቱ ለሌሎች ይልቁንም ለሕሙማን በማካፈል እንዲጠቀሙበት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
‹‹ለድኻም በጎ መሥራትን ችላ አትበል›› ምሳ.፫፥፳፯፤ ዕብ ፲፫፥፲፮

/መዝሙር ዘኒቆዲሞስ ሖረ ኃቤሁ/
ሮሜ. ፯፥፩‐፲፬
፩ኛ ዮሐ. ፬፥፲፰
የሐ.ሥ. ፭፥፴፬
ምስባክ፡-
መዝ ፲፮፥፫
ሐውጽከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ
አመከርከኒ ወኢተረክበ ዐመፃ በላዕሌየ
ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው
ትርጉም
በሌሊት ጎበኘኸኝ ልቡናዬንም ፈተንከው፡፡
ፈተንከኝ በላዬ ምንም በደል አልተገኘም
የሰው ልጅ ስራን አፌ እንዳይናገር፡፡
ምንጭ
ምስባክ ቃለ ሕይወት ሊቀ ጽጉሃን ኄለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሰባቱ አጽዋማት ተስፋዬ ምትኩ

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro