በእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ

ባረክናክሙ እም ቤተ እግዚአብሔር

በእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ

መዝ ፻፲፯፥፳፮

በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ የሰንበት ት/ቤቱ አባላት መመረቃቸውን ምክንያት በማድረግ በአይነቱ ልዩ የሆነ መርሃ ግብር እሁድ ሐምሌ ፩፮ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ጠዋት ከቅደሴ መልስ አዘጋጅቷል፡፡

በዕለቱ በቀለም ትምህርታቸው ወይንም ከመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ ከ፷፪ ለማያንሱ አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ መርሃ ግብር እየተዘጋጀ መሆኑን በመረጃ ስርዓትና ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ የግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡

የመርሃግብሩ ዋና ዓላማ፤

  • ተመራቂዎች የበለጠ ደረጃ ለመድረስ እንዲተጉ ማበረታታት፤
  • ተመራቂዎች በተማሩት ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን ፣ ለሀገር እንዲሁም ለወገን የሚጠቅም ሥራ እንዲሠሩ አደራ መስጠት እና
  • በእነርሱ እግር የሚተኩ ታናናሽ ወንድምና እህቶቻቸውን ማበረታታት ነው፡፡

በዚህ መርሃ ግብር ላይ የተመራቂ ቤተሰቦች እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት የሚሳተፉ ሲሆን፤በበዓሉ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳማችን አስተዳዳሪ እና አገልጋይ ካህናትና ዲያቆናት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

 

 

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro