መጻጉዕ (፬ኛ ሳምንት)

 

 
መጻጉዕ
ወንጌል፡- ዮሐ ፭.፩-፲፯
‹‹ከዚህም በኋላ በአይሁድ በዓል እንዲህ ሆነ፡- ጌታ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፣ በኢየሩሳሌም ድኅነት የሚገኝባ መጠመቂያ ነበረች፡፡ ስሞዋንም በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል የበጎች መዋኛ ማለት ነው፡፡ አምስት እርከኖች ነበሩአት፣ ከዚያም ብዙ ድውያን ፤እውሮች አንካሶች የሰለሉ፤የደረቁ እግረ አባጦች፣ልምሾች ተኝተው የውሃውን መታወክ ይጠባበቁ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ መጠመቂያው ወርዶ ውሃውን በሚያናውጠው ጊዜ ከውሃውም መታወክ በኋላ መጀመሪያ ወርዶ የሚጠመቅ ካለበት ደዌ ሁሉ ይፈወስ ነበርና፡፡ ከዚያም ከታመመ ሰላሳ ስምንት ዓመት የሆነው አንድ ሰው ነበር፡፡ ጌታ ኢየሱስም ያን ሰው ከአልጋው ተጣብቆ ዐየና በደዌ ታስሮ ብዙ ዘመን እንደ ቆየ ዐወቆ ልትድን ትወዳለህን አለው፡፡ ድውዩም አዎን ጌታዬ ግን ውሃው በተናወጠ ጊዜ ወደ መጠመቂያው የሚያወርደኝ ሰው የለኝም፤ እኔ በምመጣበት ጊዜም ሌላውም ቀድሞኝ ይወርዳል አለው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ተነሥና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለው፡፡ ያንጊዜም ያ ሰው ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሔደ፤ያቺ ቀንም ቅዳሜ ነበረች፤ አይሁድም የዳነውን ሰው ዛሬ ሰንበት ነው አልጋህን ልትሸከም አይገባህም አሉት፡፡ እርሱም መልሶ ያዳነኝ እርሱ፤ አልጋህን ተሸክመህ ሒድ አለኝ አላቸው፡፡ አይሁድም አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ያለህ ሰውዬው ማነው ብለው ጠየቁት፡፡ ያ የተፈወሰው ግን ያዳነው ማን እንደሆነ ዐላወቀም፡፡ ጌታ ኢየሱስ በዚያ ቦታ በነበረበት በብዙ ሰዎች መካከል ተሰውሮ ነበርና ከዚህም በኋላ ጌታ ኢየሱስ ያን ያዳነውን ሰው በምኩራብ አገኘው፡፡ እነሆ! ድነሀል ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ዕወቅ አለው፡፡ ያም ሰው ሔዶ ያዳነው ጌታ ኢየሱስ እንደሆነ ለአይሁድ ነገራቸው፡፡ ስለዚህ አይሁድ ጌታ ኢየሱስን ያሳድዱት ሊገድሉትም ይሹ ነበር፤በሰንበት እንዲህ ያደርግ ነበርና፡፡››
ዋና መልዕክት
•እግዚአብሔር ሕሙማንን በምህረቱ ይጎበኛቸዋል፡፡ ከደዌአቸውም ፈውሶ ጤንነታቸውን ሊመልስላቸው ይችላል፡፡
•እግዚአብሔር በደዌያት ላይ ሥልጣን አለው፡፡ ያለውጣ ውረድ ያድናል፣ የዳነ ሰውም አዳኙን ማወቅ፣ ውለታውን በደግ መመለስ ይገባል፡፡
ተጨማሪ መልእክት፡-
•ሰው በደረሰበት ችግር ላይ የባሰ ችግር እንዳያጋጥመው እግዚአብሔርን ማሰብ ይገባዋል፡፡ ኅብረተሰቡም ምነም ምክንያት ሳያደርግ በሽተኞችን ለመርዳት በጋራ መወያየት ይገባዋል፡
‹‹ ሰዎችም በአልጋ ተሸክመው ልምሻ የሆነ ሰው አመጡ፤… ጣራውን አፈረሱና ከነአልጋው ወደ ቤቱ ውስጥ አውርደው በጌታ ፊት አኖሩት፡፡››
ሉቃ.፲፰-፳፩፣ ፊል.፪.፫

/መዝሙር ዘመጻጉዕ አምላኩሰ ለአዳም/
ገላ.፭፥፩
ያዕ.፭፥፲፬
የሐ.ሥ ፫፥፩-፲፪
ምስባክ፡-መዝ ፵፥፫
እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ
ወይመይጥ ሎቱ ኩሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ
አንሰ እቤእግዚኦ ተሳሃለኒ
ትርጉም፡-
እግዚአብሔር ከታመመበት አልጋ ሳለ ይረዳዋል
መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል፡፡
እኔስ አቤቱ ይቅር በለኝ እላለሁ፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ለዓለመ ዓለም አሜን!!!
ምንጭ
ምስባክ ቃለ ሕይወት ሊቀ ጽጉሃን ኄለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሰባቱ አጽዋማት ተስፋዬ ምትኩ

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro