ሆሣዕና(፰ኛ ሳምንት)


ሆሣዕና

ወንጌል ዮሐ.፲፪፥፲፩‐፳

‹‹በማግስቱም ለበዓል መጥተው የነበሩ ብዙ ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመጣ በሰሙ ጊዜ የሰሌን ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው ሆሣዕና በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የባሕርይ አምላክ ነው፤ የእስራኤልም ንጉስ ነው፤ እያሉ ወጥተው ተቀበሉት፡፡ጌታ ኢየሱስም የአህያ ግልገል አግኝቶ በእስዋ ላይ ተቀመጠ፡፡ ‹‹የጽዮን ልጅ አትፍሪ እነሆ! ንጉስሽ በአህያ ግልገል ተቀምጦ ይመጣል፡፡›› ተብሎ እንደተፃፈ፡፡ ጌታ ኢየሱስ ከተገለጠበት ጊዜ በቀር ቀድሞስ ደቀ መዛሙርቱም ይህን ነገር ዐላወቁም ነበር፤ያን ጊዜ ግን ይህ ስለ እርሱ እንደተጻፈ አሰቡና እንዲህ አደረጉለት፡፡ ከዚያም አብረውት የነበሩት እነዚያ ሕዝብ አልዓዛርን ከመቃብር እንደጠራው ከሙታንም ለይቶ እንደ አስነሳው መሰከሩለት፡፡ ስለዚህም ነገር ሕዝቡ ሁሉ ሊቀበሉት ወጡ፤ ይህን ተአምራት እንደ አደረገ ሰምተዋልና፡፡ ፈሪሳውያንም እርስ በርሳቸው ምንም ምን የምትረቡት የምትጠቀሙት እንደሌለ ታያላችሁን እነሆ! ዓለም ሁሉ ተከትሎታል አሉ፡፡››

ዋና መልእክት

  • እግዚአብሔር ነኝ ብሎ የሚመጣ የባሕርይ አምላክ ነው እርሱም በሥጋ ማርያም ተገለጠ፡፡ የትሕትና መምህርም ሆነ፡፡
  • እግዚአብሔርን ከድንቅ ስራው የተነሳ ማመን፣መመስከር በትህትና ማመስገንም እውነተኛነት ነው፡፡

ተጨማሪ መልእክት፡-

  • ከሰው አቅም በላይ የሆነ ማናቸውም ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ሊወገድ ይችላል፤ እውነተኛው መድኃኒትም እርሱ ስለሆነ ሰው በሚደርስበት ህመም ተስፋ እንዳይቆርጥ መምከር ማጽናናትም ወገንን መርዳት ነው፡፡

‹‹በጊዜውም ያለ ጊዜውም ምከር፣አስተምር፣ አረጋጋ፣ አጽናና›› ፩ኛ ጢሞ.፬፥፪ የሐ.ሥ. ፲፬፥፳፪

/መዝሙር ዘሆሣዕና ወእንዘ ሰሙን/

ዕብ ፰፥፩
፩ኛ ጴጥ.፩፥፲፫‐፲፩
የሐ.ሥ.፰፥፳፮
ምስባክ፡-

መዝ ፻፲፯፥፳፮

ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር

ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር

እግዚአብሔር እግዚእ አስተርአየ ለነ

ትርጉም፡-

በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ምስጉን ነው፡፡

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ ጌታ እግዚአብሔር ተለገጠልን፡፡

ምንጭ
ምስባክ ቃለ ሕይወት ሊቀ ጽጉሃን ኄለ ጊዮርጊስ ዳኘ
ሰባቱ አጽዋማት ተስፋዬ ምትኩ

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro