ማውጫ

ቀዳሚ ገጽ

በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት እንደ ተለመደው በ2010 ዓ.ም አዳዲስ  ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቆ ተመዝጋቢዎችን እየጠበቀ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህ መንፈሳዊ ትምህርት ቅዳሜ እና እሑድ የሚሰጥ ነው፡፡ በተጨማሪ ቅዳሜ መምጣት ለማይችሉ እሑድ ብቻ የሚሰጥ መርሐ ግብር አለ፡፡ ትምህርቱ የሚጀምረው ጥቅምት 4/2010 እንደሆነ የሰንበት ት/ቤቱ፣ ትምህርትና ሥልጠና ሥራ አስፈጻሚ አሳውቋል፡፡ ይህ መንፈሳዊ ትምህርት ቅዳሜ እና እሑድ የሚወስዱ በአንድ ዓመት የሚያልቅ ሲሆን፤ እሑድን ብቻ የሚወስዱ ደግሞ በሁለት ዓመት ይጠናቀቃል፡፡

የተምሮ ማስተማር ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ትምህርት ለምዕመኑ ሲሰጥ ረጅም ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን የሁለት ሺ ዘጠኝ ዓመት 31 ያህል ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ 0913475201/0912094605 ይደውሉ!

ወስብሀት ለእግዚአብሔር

                     ©2017.Temro Mastemar - All Rights Reserved. Website by Temro